የዓለም ዋንጫ ንግርቶች

Translated into Afrikaans (Original version)


ጳውሎስ ኦክቶፐስ የተባለውን ዓሣ ታስታውሳላችሁ? በጀርመን የተካሄዱትን ጫዋታዎች መተንበይ የቻለ፥ የ 2010 የዓለም ዋንጫ ኮከብ ነበር። የመጨረሻውንም ጫወታ አሸናፊ ደግሞ ተንብዮአል። ትንበያውን የጀመረው በ2008 የአውሮፓ ዋንጫ ላይ ሲሆን፥ ከ 13 ጫዋታዎች ውስጥ 11 በትክክል ተንብዮአል። በእያንዳንዱ ጫዋታዎች ላይ የሚሳተፉትን የቡድኖቹን ባንዲራ እና ምግብ የያዙት ሣጥኖችን በመምረጥ ይተነብይ ነበር። እንደአጋጣሚ ሆኖ፥ በ2010 መጨረሻ ላይ ሞተ።

ጳውሎስ ብቻውን አልነበረም። ሐር የተባለውም አዞ የ2010 የዓለም ዋንጫ አሸናፊውን ተንብዮአል። በተጨማሪም፥ የአውስትራሊያ የፈዴራላዊ የምርጫ ውጤቶችን በተከከታታይ ለሁለት ጊዜ መተንብ ችሎአል። ሆኖም ግን፥ የጀርመኑ ዓሣ ያህል ትኩረት አልሳበም። ማኒ የተባለውም የሲንጋፖር በቀቀን፥ የ2010ን የዓለም ዋንጫ ጫዋታችን  በሙሉ እስከ ሩብ ፍጻሜ እና ግማሽ ፍጻሜ ድረስ በትክክል የተነበየውም ቢሆን፥  የመጨረሻውን ጫዋታ በስፔን እና በኔዘርላድ መካከል ማን ውጤታማ እንደሚሆን መተንበይ ስላልቻለ የተሻለ ሥራ አልሠራም።

ጳውሎስ የተባለው ዓሣ ያለጊዜ ከተለየ ጊዜ ጀምሮ፥ የእርሱን ዝና ለመውሰድ ከፍተኛ ፍክክር እየተደረገ ነው። በ2012 የአውሮፓ ዋንጫ ጫዋታ ጊዜ፥ ይህን ጫዋታ የተጫወቱ ሦስት እንሰሳቶች ነበሩ። ሲታ የተባለ፥ በፖላንድ ውስጥ ክራኮው በተባለው የእንሰሳት መኖሪያ ውስጥ የሚኖር የሕንድ ዝሆን። ፍሬድ የተባለ፥ የዩክሬን አውሬ ትዊቴር በተባለው ማኅበራዊ ድኅረገጽ ላይ መከታተል የሚቻለው እና ፉቲክ የተባለው፥ የዩክሬን ትንበያ ሰጪ ዓሣማ ከሦስት ጫዋታዎች ውስጥ 2ቱን በትክክል ተንብዮአል።

በሚቀጥለው የዓለም ዋንጫ ጫዋታ ጊዜ፥ ጳውሎስ ኦክቶፐስ የተባለውን ዓሣ ቦታ የሚወስደስ ማን ነው? በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በጳጳስ ፍራንሲስ የተባረከችው፥ አሁን የኢጣሊያን ብሔራዊ የሕዝብ ትንበያ የምትሠራው በቀቀን ትሆን? ወይም እስከ ዛሬ ከ33 ጫዋታዎች ውስጥ 30ውን ውጤት በትክክል የተነበየው ኔልይ የተባለው የጀርመን ዝሆን ይሆን? በእርግጥ፥ በቻይና የመንግሥት ሚዲያ ድጋፍ የሚደረግለት የቻይና ድብን የሥነ ልቦና ኃይልንም መናቅ ተገቢ አይደለም።

አሞሬ የተባለው የኢጣሊያን በቀቀን (የኢጣሊያ ነዋሪዎች ለፍቅር) በትንሹ የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ ላይ የሚያሸንፈውን ቡድን ባንድራ በመምረጥ ትንበያውን ሰጥቶአል። ኔልይ ደግሞ የተፎካካሪዎቹ አገሮች ባንዲራዎች ፊት ባሉት ጎሎች ውስጥ ኳሷን በምመታት አሸናፊውን ለመተንበይ መርጦአል። ከዚያ ይልቅ፥ የቻይናው ድብ ደግሞ የቡድኖቹ ጫዋታዎች በሚደረጉበት ጊዜ በባንዲራ ምልክት ከተደረገባቸው ሳጥኖች ውስጥ ምግብ በማንሳት እና በጥሎ ማለፍ ጊዜ ደግሞ ባንዲራው የሚውለበለብበት ዛፍ ላይ በመውጣት የጫዋታዎቹን ውጤት ይተነብያል።

ለማዳ የቤት እንሰሳ አልዎት?
እርሱ ወይም እርሷ የተሻለ መሥራት ይችላሉ? እንዴት?
እስቲ እንዲተነብዩ ዕድሉን እንስጣቸው!

by Alemu Zegeye

236 Votes
#49 of #1440 in the World
#1 of #9 for AfrikaansGo to the ranking page for Afrikaans

Can you translate better?

Join the challenge